company-logo

Senior Machine Operator

Minaye PLC

job-description-icon

Low and Medium Skilled Worker

Heavy Machinery Operation

Addis Ababa

5 Positions

2025-12-20

to

2025-12-27

Required Skills

electricity

Fields of study

General Mechanic/Industrial Technology

Full Time

Share

Job Description

ብዛት፡ 5

ዋና ሃላፊነቶች፡

  • በተመደበበት የሥራ ቦታ በሰዓቱ መገኘትና ተገቢውን የሥራ ልብስና የአደጋ መከላከያ በማድረግ ይዘጋጃል፤

  •  የተመደበበትን የማምረቻ ማሽኑንና አካባቢውን ያጸዳል፣ ማሽኑን ያሟሙቃል፤

  • ተቀጽላዎችንና ግብዓቶችን በማሟላት፣ ማሽኑ በትክክል የሚሠራ መሆኑን በማጋገጥ የምርት ትዕዛዝ ይቀበላል፤

  • ለሚፈለገው ምርት የሚሆነውን ግብአት በተገቢው መጠን እንዲቀርብ በማድረግ በማምረቻ ማሽኑ ላይ ይጭናል፤

  • በትዕዛዙ መሠረት ሥራውን ለመጀመር አስፈላጊው ሁሉ መሟላቱን መስተካከሉን በማረጋገጥ ማሽኑን ያስነሳል፤

  • የምርቱን ሂደት፣ ጥራትና ደረጃ እንዲሁም የማሽኑን ደህንነት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ልዩነቶች ሲከሰቱ ያስተካክላል፤

  • ያመረተውን ምርት ጽዳትና ደህንነቱን ጠብቆ እንደሁኔታው ያስረክባል ወይም ለሚቀጥለው የምርት ሂደት በተገቢው ሥርዓት ያስተላልፋል፣ በተከታታይ የምርት ሂደት የሚተላለፍ ከሆነም በሚፈለገው ሁኔታ መተላለፉን ይከታተላል ያረጋግጣል፤

  • የማምረቻ የማሽኑን የምርት ሰዓትና መጠን እንዲሁም የምርት ግብዓቶች ዓይነትና መጠን በተገቢው ቅጽ ይመዘግባል፤

  • በምርት ሂደት በሰው ሕይወትና ንብረት አደጋ እንዳይደርስ ተገቢውን ጥንቃቄና ክትትል ያደርጋል፤

  • የማሽን ብልሽት ሲያጋጥም ያስተካክላል ወይም ከአቅም በላይ ከሆነ ለቅርብ አለቃው በማሳወቅ እንዲጠገን ያደርጋል፤

  • ማሽኑ በጥገና ባለሙያዎች በሚጠገንበት ጊዜ አብሮ ይሠራል፤

  • ማሽኑ በማይሰራበት ጊዜ በውሃ እንዲታጠብና ተገቢው ዘይትና ቅባት እንዲደረግበት እንዲሁም አካባቢው እንዲፀዳ ያደርጋል፤

  • በተጨማሪም ሌሎች ከቅርብ ሃላፊው የሚሠጡ የስራ ትዕዛዞችን ያከናውናል፡፡

የስራ መስፈርቶች:

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ ኮሌጅ 10+3 ያለው/ያላት

  •  የትምህርት ዓይነት፤ በጠቅላላ መካኒክ ወይም ኢንዱስትሪያል ኤሌክትርክሲቲ

  • የሥራ ልምድ: በዲፕሎማ 5 ዓመት ወይም 10+3 7 ዓመት ያለዉ/ያላት በፓኬጂንግ ኢንዱስትሪ የሰራ / የሰራች

የማመልከቻ መመርያ፡

  • አመልካቾች ዋናውን የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ በኢሜል፡ hcminayee@gmail.com በመላክ ማመልከት ይችላሉ።

  • ማስታወሻ፦ ከዚህ በፊት በከለር ማሽን ኦፕሬተርነት የሰራ/የሰራች ቢሆን ይመረጣል።

Fields Of Study

General Mechanic/Industrial Technology

Skills Required

electricity