Job Requirement
- የሚፈለገው የትምህርት ደረጃ :- ፒኤችዲ/ኤምኤስሲ/ ቢኤስሲ ዲግሪ በውኃ ምህንድስና ወይም በተመሳሳይ
- የሥራ ልምድ :- 6/8/10 ዓመት በውሃ፣ በግድብና በመስኖ ሥራ ላይ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ያለው/ያላት ከዚህ ውስጥ 4 ዓመት በኃላፊነት የሰራ/ች
- የደመወዝ ደረጃ :- 16 መነሻ
- የደመወዝ መጠን :- 20,965
- የሥራ ቦታ :- በኮርፖሬሽኑ ባሉ የውኃና ግድብ ሥራ ፕሮጀክቶች
ጥቅማ ጥቅሞች :-
- ለፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ፡ – የኋላፊነት አበል፡- 9500 ብር፣የሙያ አበል የደመወዙን 55%፣የተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) አበል፣ገደብ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት ፣የ24 ሰዓት የሕይወት መድን ዋስትና እና በሀገር ውስጥ 100% የህክምና ሽፋን
ማሳሰቢያ፡-
- የሥራ ልምድ ከተጠየቀው ትምህርት ደረጃ በኋላ የተገኘ ብቻ ይሆናል፡፡
- የቅጥር ሁኔታ በኮንትራት ሆኖ የሥራ አፈፃፀም ብቃት እየታየ ቋሚ የሚደረግ፡፡
- አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማለት በተጠቀሰው የሙያ መስመር አገልግሎት ሲሆን፣ የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስረጃ የሥራ ግብር ስለመከፈሉ፣ ደመወዝና አገልግሎት ከመቼ እስከ መቼ እንደተሰጠ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
How to Apply
አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ የትምህርትና ሥራ ልምድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የሰው ሃብት አስተዳደር ቡድን 1 ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ህንፃ ወይም ከበሻሌ ሆቴል ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ